የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሥራቸው ላይ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን 'አዲስ ፎርቹን' ዘገበ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-14 03:44:42 UTC
AdYour ad here[email protected]

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሥራቸው ላይ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን 'አዲስ ፎርቹን' ዘገበ። የአየር መንገዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሰብሳቢነት የአቶ መስፍን ጣሰውን የሥራ ዘመን ማራዘሙ ተገልጿል። አቶ መስፍን በቅርብ በሰጡት መግለጫ፣ ጡረታ መውጣት የነበረባቸው ከ3 ዓመት በፊት የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ ለ2 ዓመት ከዚያ ለ1 ዓመት የስራ ውላቸው መራዘሙን ተናግረው ነበር። አሁንም ለተጨማሪ አንድ ዓመት ኃላፊነታቸው መራዘሙን 'አዲስ ፎርቹን' ከእሳቸው ማረጋገጡን ገልጿል። @tikvahethiopia

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]