❗️በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደውን ውጊያ ተከትሎ የደሴ-ወልዲያ መንገድ ከትናንት ጀምሮ እንደተዘጋ ዋዜማ ሠምታለች፡፡

ADDIS_NEWSneutral2026-11-02 19:20:56 UTC
AdYour ad here[email protected]

❗️በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በአምባሰል ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የሚካሄደውን ውጊያ ተከትሎ የደሴ-ወልዲያ መንገድ ከትናንት ጀምሮ እንደተዘጋ ዋዜማ ሠምታለች፡፡ በውጫሌ ከተማ ከቅዳሜ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በከባድ መሳሪያዎችና በድሮን የታገዘ ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረውናል። ዛሬ ሠኞ በከተማዋ ልዩ ሥሙ "ዳንካ ሚካኤል" በተባለ ሥፍራ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃቶች እንደተፈጸሙና ኾኖም በወቅቱ በንጹሃን ላይ የደረሠ ጉዳት ስለመኖሩ በእርግጠኝነት መናገር እንደማይችሉ ነዋሪዎቹ ገልጸውልናል። በሌላ በኩል፤ በሀብሩ ወረዳ ውርጌሳ እና ጊራና ገጠራማ አካባቢዎችም በሁለቱ ወገኖች መካከል ውጊያ መቀጠሉን ተረድተናል፡፡ @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]