ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማቀላቀል ሥራ በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ ነው አለ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፡፡
ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማቀላቀል ሥራ በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ ነው አለ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን፡፡ ኮሚሽኑ ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል ጋር በመተባበር ከስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋም የሚያስችል የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል። የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የዜጎችን ክብርና ደህንነት ማዕከል ያደረገ የዲፕሎማሲ ትብብር ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡ ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመለሱ ዜጎችን በክብርና በደህንነት መቀበልና መደገፍ የመንግሥትን ዜጋ ተኮር አስተዳደር አቅጣጫ የሚያሳይ ተግባራዊ ሥራ ነው ብለዋል፡፡ ሰብዓዊ ድጋፍን ይበልጥ ለማሳደግ ከልማት አጋር ተቋማት ጋር የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክተዋል፡፡ በዚህ የትብብር ማዕቀፍ የኪንግ ሳልማን…
Read the full story at zena24now ↗