የሥራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-08-14 08:28:41 UTC
AdYour ad here[email protected]

የሥራ ቡድኖች የአጀንዳ ምክረ ሃሳቦቻቸውን ለሚያደራጀው ቡድን እያቀረቡ ነው። የሥራ ቡድኖች ሁሉም ቡድኖች ያዘጋጇቸውንና የተስማሙባቸውን ምክረ-ሀሳቦች እንዲያናብብ፣ እንዲያጣጥም እና እንዲያደራጅ ለተቋቋመው እና 120 አባላት ላሉት ቡድን በማቅረብ ላይ ናቸው፡፡ ይህ ቡድን ከስምንቱ ባለ 500 አባላት የሥራ ቡድን በተመረጡ 15 አባላት የተዋቀረ ሲሆን መግባባት የተደረሰባቸውን የሁሉንም አጀንዳዎች ምክረሃሳቦች አዳምጦ የሚያጣጥም፣ በሚቀርቡ ሀሳቦች መካከል መጣረስ እንዳይኖር ጥንቃቄ የሚያደርግና ለጠቅላላ ሀሳቦቹ ወጥነት በመፍጠር 4ሺ አባላት ላሉት ዋናው ጉባኤተኛ አደራጅቶ የሚያቀርብ ነው፡፡ ቡድኑ በአሁኑ ሰዓት ከእያንዳንዱ የሥራ ቡድን የመጡ ምክረሃሳቦችን በማዳመጥ ላይ ነው፡፡ መረጃው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው። #AMECO #Nationaldialogue #Ethiopia🇪🇹…

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]