የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬዳዋ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራን አስጀመረ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በድሬዳዋ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራን አስጀመረ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ረሻድ ከማል በድሬዳዋ ከተማ በያዝነው ክረምት በኮርፖሬሽኑ የሚከናወኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ከድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከክቡር አቶ ከድር ጀዋር ጋር በጋራ በመሆን አስጀምረዋል። ኮርፖሬሽኑ በዘንድሮው የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሩ ለአቅመ ደካማ ወገኖች የመኖሪያና የንግድ ቤት ግንባታ፣ የችግኝ ተከላ፣ የጤና መድህን ሽፋን እንዲሁም የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ሥራውን በይፋ አስጀምሯል። የአቅመ ደካማ ወገኖችን ተጠቃሚ የሚያደርገውና በከተማ አስተዳደሩ ወረዳ 6 አካባቢ የሚገነባው የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶች ግንባታ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ ቤቶቹ አስፈላጊውን መሠረታዊ አገልግሎት አሟልተው በጥራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ…
Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗