በጃፓን በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ምክኒያት የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአውሮፕላን ማረፊያ መውጣት አልቻሉም ።
በጃፓን በጣለ ከፍተኛ ዝናብ ምክኒያት የአራት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአውሮፕላን ማረፊያ መውጣት አልቻሉም ። በምስራቅ ጃፓን በጣለው “ታይቶ በማይታወቅ” ከባድ ዝናብ ምክኒያት ቢያንስ የአራት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ 7 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በቶኪዮ ናሪታ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲቆዩ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመንግስት ህንፃዎች ውስጥ ተጠልለው እንዲያድሩ አስገድዷል ። ሐሙስ ምሽት ከቶኪዮ በስተምስራቅ በምትገኘው ቺባ ግዛት ላይ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ የመሬት መንሸራተት ስጋት እና የኤሌክትሪክ መቆራረጥንም አስከትሏል። በቺባ እና በሌሎች አካባቢዎች ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ የተላለፈ ሲሆን 45 ሺህ ያህል ቤቶች የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጦባቸዋል። በዛሬው እለት ዝናቡ ቢቀንስም ባለስልጣናት ግን በአካባቢው ስላለው የጎርፍ…
Read the full story at addis_news ↗