የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ በናይሮቢ በቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት ተዘጋ።
የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ በናይሮቢ በቤት ኪራይ ዕዳ ምክንያት ተዘጋ። በኬንያ ናይሮቢ የሚገኘው የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ የአራት ወራት የቤት ኪራይ ባለመክፈሉ ምክንያት ከማክሰኞ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ ተዘግቧል። የኤምባሲው ሠራተኞች እና ፓስፖርት ወይም የጉዞ ሰነድ ለማግኘት ወደ ቦታው የሄዱ ዜጎች በሩ ተዘግቶባቸው መመለሳቸውን ተናግረዋል። መንግሥት አፋጣኝ መፍትሔ እስኪሰጥ ድረስም ኤምባሲው ተዘግቶ እንደሚቆይ ታውቋል። የሲቪክ ማህበራት መሪዎች ይህ ዕዳ መከፈል አለመቻሉ የሀገሪቱን ገጽታ በእጅጉ እንደሚጎዳ ገልጸዋል። በመሆኑም የደቡብ ሱዳን መንግሥት በውጭ ሀገር ለሚገኙ ኤምባሲዎች በጀት በመመደብ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አሳስበዋል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗