የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው የቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሃት ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-15 17:11:43 UTC
AdYour ad here[email protected]

የትግራይ እና አማራ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው የቆቦ አካባቢዎች ዛሬ ማለዳ በኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት እና በሕወሃት ታጣቂዎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ነዋሪዎቹ እንዳሉት በቆቦ ጮቢ በር እና አዲስ ቅኝ በተባሉ አካባቢዎች ማለዳ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ የተጀመረው ዉጊያው ከአንድ ሰዓት በኋላ ጋብ ብሏል።በግጭቱ የአነስተኛ እና መካከለኛ የጦር መሳሪያዎች ድምጽ ይሰሙ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች የከባድ መሳሪያ ድምጽ በዉጊያው ውስጥ አለመሰማቱን ተናግረዋል። ግጭቱ ከዋጃ አካባቢ ዋልካ መንደር መቀስቀሱን የገለጹት ነዋሪዎች ግጭቱን ተከትሎ ከቆቦ ወደ አላማጣ የሚወስደው ዋና መንገድ ለጊዜው ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ከረፋዱ 4:00 በኋላ እንደገና ለተሽከርካሪ ክፍት መሆኑን ተናግረዋል። Via DW @Addis_News @Addis_News

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]