ኢትዮጵያ ውስጥ የደስተኛ ሕይወት ጣሪያ ላይ ለመድረስ በነፍስ ወከፍ የሚያስፈልገው አማካይ ገቢ ከ123 አገራት ዝቅተኛው መኾኑን አንድ ጥናት አመለከተ።
ኢትዮጵያ ውስጥ የደስተኛ ሕይወት ጣሪያ ላይ ለመድረስ በነፍስ ወከፍ የሚያስፈልገው አማካይ ገቢ ከ123 አገራት ዝቅተኛው መኾኑን አንድ ጥናት አመለከተ። ኢትዮጵያ ውስጥ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር 10 ሺሕ 176 ዶላር ገቢ እንደሚያስፈልግ ሪሚትሊ የተባለ ዓለማቀፍ ኩባንያ ባደረገው ጥናት ገልጧል። ናይጄሪያና ሩዋንዳ ከ15 ሺሕ ዶላር በታች በኾነ ገቢ ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ ይዘዋል። ከአፍሪካ ከፍተኛው 59 ሺሕ 675 ዶላር ገቢ የተመዘገበባት ግብጽ ስትኾን፣ በጥናቱ የተካተቱት 32 የአፍሪካ አገራት አንዳቸውም ከ100 ሺሕ ዶላር ገቢ አልደረሱም። በአገራት መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዲታይ አስተዋጽዖ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል፣ ዶላር መግዛት የሚችለው ምርትና የውጭ ምንዛሬ ተመን መለያየት ተጠቅሠዋል። @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗