ሰላም ለሁሉም ናት፤ ስለሰላም ሁሉም ያገባዋል !

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-08-16 05:50:25 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሰላም ለሁሉም ናት፤ ስለሰላም ሁሉም ያገባዋል ! በአማራ ክልል ከ2015 ዓ.ም መገባደጃ ጀምሮ የተከሰተው የሰላም እጦት ጥሎት ያለፈው ጉዳት ጥልቅ እና ሁለንተናዊ ነው። ክልሉ የሀገሪቱ የግብርና ምርት የጀርባ አጥንት በመኾኑ ግጭቱ የንግድ መስመሮችን ዘግቶ፣ የግብዓት ሥርጭትን አጓድሎ እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱን አቀጭጮ የኑሮ ውድነቱን ለሸማቹ ፈተና እንዲኾን አድርጎት ቆይቷል። በትምህርት እና በጤና ተቋማት መዘጋት፤ በዜጎች መፈናቀል፣ በትውልዱ ላይ በሰፈነው ስጋት እና ጭንቀት ሳቢያ ማኅበራዊ እና ሥነ-ልቦናዊ መስተጋብሩ ክፉኛ ተጎድቷል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ስጋት ውስጥም ቢኾን የሕዝቡ የሥራ ወኔ እና የማይበገር ተስፋ አልተሰበረም። አርሶ አደሮች እና ነጋዴዎች ላባቸውን እያፈሰሱ ያስመዘገቧቸው የልማት ውጤቶች ለነገው ብሩህ ቀን ያለውን ጽናት የሚያሳዩ ህያው ምስክሮች በመኾን…

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]