ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኾነው ተሾሙ።

AMHARAMASSMEDIAneutral2026-08-17 07:32:52 UTC
AdYour ad here[email protected]

ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኾነው ተሾሙ። የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ አድርገው ሾመዋል። በሌላ በኩል የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት ኮሚሽነር ጄነራል ዘላለም መንግሥቴ (ዶ.ር) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ኾነው መሾማቸው ታውቋል። የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ለሁለቱም ከፍተኛ መሪዎች የሥራ ዘመናቸው ስኬታማ እንዲኾን ተመኝቷል። #አሚኮ_አማራ_ፖሊስ #ባሕር_ዳር #ነሐሴ_11_2018_ዓ_ም የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Read the full story at amharamassmedia ↗
AdYour ad here[email protected]