10 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሬዝዳንትነት ቦታቸውን ለግልጽ ውድድር ክፍት ሊያደርጉ ነው፡፡
10 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የፕሬዝዳንትነት ቦታቸውን ለግልጽ ውድድር ክፍት ሊያደርጉ ነው፡፡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ምልመላ፣ ምርጫ እና ምደባ የሚመራበት አዲስ መመሪያ አፅድቆ ወደ ትግበራ ለመግባት ዝግጅት ማጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል። ባለፉት ሁለት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች የአመራር ክፍተት እንዳይፈጠር ፕሬዝዳንቶች በተጠባባቂነት ሲመደቡ መቆየታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡ አሁን ላይ ለትግበራ ዝግጁ በሆነው አዲሱ መመሪያ መሰረት "የፕሬዝዳንትነት ቦታዎች ግልጽ፣ ፍትሃዊ እንዲሁም በብቃትና በውድድር ላይ በተመሠረተ ሂደት የሚሞሉ ይሆናል" ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተጠባባቂ ፕሬዝዳንቶች የሚመሩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የፕሬዝዳንቶቻቸው የሥራ ዘመን ያበቃ ወይም የምርጫ ሒደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚያበቃ ዩኒቨርሲቲዎች በውድድር ሒደቱ እንደሚካተቱ ትምህርት ሚኒስቴር…
Read the full story at addis_news ↗