ትራምፕ ካይሮንና አዲስ አበባን ማስታረቅ ይፈልጋሉ
ትራምፕ ካይሮንና አዲስ አበባን ማስታረቅ ይፈልጋሉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የዓረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቦውሎስ እንዳሉት፤ ዶናልድ ትራምፕ በናይል ወንዝ ተፋሰስ አገሮች መካከል የውሃ አጠቃቀም ስምምነት እንዲደረስና የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ውዝግብ እንዲፈታ ካይሮንና አዲስ አበባን ማስታረቅ ይፈልጋሉ። ዋሽንግተን ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄዎችን እንደምትፈልግ እና ከሁሉም ወገኖች ጋር ንግግሮች መቀጠላቸውን የገለጹት አማካሪው፣ ግብፅና ኢትዮጵያ ሁሉንም አገሮች የሚያረካ ስምምነት ላይ ለመድረስ በውይይት እንዲሳተፉ አሜሪካ ማበረታታቷን እንደቀጠለች ተናግረዋል። በሌላ በኩል፣ ኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን በታሪካዊ የናይል ውሃ ስምምነቶች ዙሪያ ስላሉት ውዝግቦች፤ ዋሽንግተን የሦስቱ አገሮች ባለሙያዎች በጋራ በመሥራት ለተነሱት ቴክኒካዊ ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ…
Read the full story at addis_news ↗