ድርጊቱ በጥቅምት ወር የተፈፀመ ነው
ድርጊቱ በጥቅምት ወር የተፈፀመ ነው በድብደባ ቪዲዮው ላይ ፖሊስ ምርመራ አጠናቆ መዝገቡን ለፍትህ አካል መላኩን ገለፀ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ በነበረው የድብደባ ቪዲዮ ላይ አስፈላጊው ማጣራት ተጠናቆ የምርመራ መዝገቡ ለፍትህ አካል መላኩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። የፖሊስ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ቶማስ እሸቴ ለብስራት ሬድዮ እንዳረጋገጡት፣ ድርጊቱ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በጓደኛሞች መካከል በ"ሀሜት" ምክንያት የተፈጸመ ነው። ፖሊስ ጥቆማ ይድረሰው እንጂ ቪዲዮው በማህበራዊ ሚዲያ ከሰራጨቱ በፊት ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ውለው ለሶስት ሳምንታት ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል። ኮማንደር ቶማስ አክለውም፡ህብረተሰቡ ላደረገው ጥቆማ ምስጋና አቅርበዋል። ምስሉን ቀርፆ ማሰራጨት ህገ-ወጥ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።…
Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗