በምክክር ጉባዔው በየቡድኖች የተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦችን የማጣጣም ሥራ እየተጠናቀቀ ነው

ADDIS_NEWSneutral2026-08-17 18:17:26 UTC
AdYour ad here[email protected]

በምክክር ጉባዔው በየቡድኖች የተጠናቀሩ ምክረ ሃሳቦችን የማጣጣም ሥራ እየተጠናቀቀ ነው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ም/ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ሥላሴ የሀገራዊ ምክክር ጉባዔን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም የጉባዔው ተሳታፊዎች እያንዳንዱ ቡድን 15 ተወካዮችን መርጦ በየቡድኑ ተጠናቅረው የሚገኙ ምክረ ሃሳቦችን ለማጣጣም ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡ የእነዚህ ተወካዮች ዋና ሥራ በየ ቡድኑ ብዙ ጊዜ ተፈጅቶባቸው የተዘጋጁ ምክረ ሃሳቦችን ማጣጣም መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በዚህም በ8 ቡድኖች ምክረ ሃሳቦች መካከል ተቃርኖና ድግግሞሽ ሳይፈጠር ወጥ በሆነ መልኩ እንዲቀርብ እያደረጉ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡ በተጨማሪም የተመረጡት ተወካዮች ስለ ሌሎች ቡድኖች ምክረ ሃሳቦች ግንዛቤ የወሰዱ ሲሆን ÷ በዚህም እርስ በርስ በመነጋገር ሃሳቦችን ያጣጥማሉ ነው ያሉት፡፡…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]