በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ለአዲስ ማለዳ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-18 07:08:40 UTC
AdYour ad here[email protected]

በጠለምት ወረዳ በተከሰተ ድርቅ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የመረው ቀበሌ አስተዳዳሪ ለአዲስ ማለዳ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በተከሰተው በረታች ድርቅ ሳቢያ የ16 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በመቶዎች የሚቆጠሩ የቤተሰብ አባላት ለስደት መዳረጋቸውን የመረው ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ገብረሚካኤል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። እንደ አስተዳዳሪው ገለጻ፣ በአካባቢው ከመጋቢት ወር ጀምሮ ምንም ዓይነት ዝናብ በመጥፋቱ አርሶ አደሩ የዘራው እህል ሳይበቅል ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በአካባቢው የምግብ እጥረትና ረሃብ በመከሰቱ፣ የሰው ሕይወት ከማለፉ ባሻገር የቁም እንስሳትም በሙሉ ማለቃቸውን አክለዋል፡፡ በተጨማሪም ድርቁ ያስከተለው የረሃብን ሁኔታ መቋቋም የተሳናቸው 488 አባወራዎች ከአካባቢው ለቅቀው ወደ ምዕራብ ትግራይ መሰደዳቸውን ጥላሁን አስረድተዋል። ችግሩን…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]