በኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ
በኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆኑት ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ የወንዶች የጡት ካንሰር የማይሰሩ የወተት ቱቦዎች፣ እጢዎች እና የጡት ቲሹዎች ላይ የሚከሰት የካንሰር አይነት መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ልክ እንደ ሴቶች ሁሉ የጡት ካንሰር በወንዶች ላይም በማንኛውም እድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት ይችላል ሲሉ በጳውሎስ ሆስፒታል የጡት ካንሰር ኢሜጂንግ ሰብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሜሮን አህመድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ተናግረዋል። በሴቶች ላይ ከሚከሰቱ የካንሰር አይነቶች መካከል የጡት ካንሰር ቀዳሚውና በብዛት የሚታወቅ ቢሆንም በወንዶች ላይ የሚከሰተውን የጡት ካንሰር አስመልክቶ ግን በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ ተጠቁሟል። በአለም አቀፍ ደረጃ በወንዶች ላይ የጡት ካንሰር የመከሰት እድሉ 1በመቶ እንደሚሆን ተገልጿል። በኢትዮጵያ ደግሞ የመከሰት…
Read the full story at addis_news ↗