ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ‼
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ‼ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ የሆነና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ህገ-ወጥ የሀበሻ አረቄ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲደፋ ተደረገ። የወረዳው ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ምርት፤ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የፖሊስ መርማሪዎችና አቃቤ ህግ በተገኙበት በይፋ ተወግዷል። የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለጤና ጉዳትና ለወንጀል መበራከት መንስኤ በመሆኑ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው። #WasuMohammed video 👇Like + Follow👇…
Read the full story at wasulife ↗