የጤና ሚኒስቴር በፎርሙላ ወተት አጠቃቀም እና ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው

ADDIS_NEWSneutral2026-08-18 07:37:18 UTC
AdYour ad here[email protected]

የጤና ሚኒስቴር በፎርሙላ ወተት አጠቃቀም እና ስርጭት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ሊያደርግ ነው በህጻናት ፎርሙላ ወተት አጠቃቀም፣ ስርጭት እና ማስታወቂያዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና ክትትል ከዚህ ቀደሙ የበለጠ ጥብቅ ሆኖ እንደሚተገበር ሚኒስቴሩ አስታውቋል። ጤና ሚኒስቴር እንዳለው ለዚህ ውሳኔ ምክንያት ከሆኑ ምክንያቱች መካከል ምርቶቹ ከውጭ የሚገቡ በመሆኑ በቤተሰብ እና በሀገር ደረጃ ከፍተኛ የወጪ ጫና ማሳደራቸው፣ ያለአግባብ ፎርሙላ ወተት የሚወስዱ ህጻናት ለተለያዩ የጤና እክሎች እና ለተጨማሪ የሕክምና ወጪ መጋለጣቸው፣ እናቶች የተፈጥሮ ጡት ማጥባትን እንዲተው የሚያደፋፍሩ የተጋነኑ የማስታወቂያ ዘመቻዎችን መግታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብሏል። በመሆኑም የፎርሙላ ወተት ስርጭትና አጠቃቀም በህጻናት ምግብ ቁጥጥር መመሪያ መሠረት በትክክል በሚያስፈልግባቸው አጋጣሚዎች ብቻ እንዲውል…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]