#USA⚖
#USA⚖ በአሜሪካ የ5 ዓመት ሕፃን ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ህይወቷን ያጠፋው ወንጀለኛ በገዳይ መድኃኒት መርፌ ተገደለ። በአሜሪካ አላባማ ግዛት፣ ካማሪ ሆላንድ የተባለች የ5 ዓመት ሕጻን ልጅ ላይ የግብረ ሥጋ ድፍረት ፈጽሞ ሕጿኗን በመግደሉ የተፈረደበት ጄረሚ ትሬማይን ዊሊያምስ የተባለ የ42 ዓመት ጎልማሳ ባለፈው በሞት ተቀጥቷል። ካማሪ በ2021 ከጆርጂያ ኮሎምበስ ከተማ ከቤቷ ከጠፋች በኋላ ምርመራው ወደ አላባማ ፊኒክስ ሲቲ ተስፋፋ። ፖሊስ ዊሊያምስ በሚኖርበት ቤት ፍተሻ ሲያካሂድ የሕፃኗ እቃዎች ተገኝተዋል፤ በመጨረሻም አስክሬኗ ከሕንፃው ምድር ቤት ተገኝቷል። በምርመራው መሠረት ሕፃኗ ከመገደሏ በፊት ታስራ የግብረ ሥጋ ድፍረት ተፈጽሞባት ነበር፤ በመጨረሻም በመታነቅ ሕይወቷን አጥታለች። በዊሊያምስ ስልክ ላይም ጥቃቱን የሚያሳዩ ቪዲዮዎች መገኘታቸው በፍርድ ሂደቱ ተገልጿል።…
Read the full story at addis_news ↗