በፀጉር አሠራር ውስጥ የተሸሸገ አደንዛዥ ዕፅ በሣውላ ማረሚያ ተቋም በፍተሻ ተያዘ
በፀጉር አሠራር ውስጥ የተሸሸገ አደንዛዥ ዕፅ በሣውላ ማረሚያ ተቋም በፍተሻ ተያዘ ወደ ሣውላ ማረሚያ ተቋም በድብቅ ሊገባ የነበረ ህገ-ወጥ አደንዛዥ ዕፅ የደህንነት አባላት ባደረጉት ጥብቅ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የተቋሙ አዛዥ አስታወቁ። ወ/ሮ ዋሉሎ ቦንኬ የተባለች ተጠርጣሪ ወደ ማረሚያ ቤቱ እንዳይገባ በጥብቅ የተከለከለ አደንዛዥ ዕፅ በጥንቃቄ በመጠቀል በፀጉር አሠራሯ ውስጥ ደብቃ ለማስገባት ሞክራ ነበር። ሆኖም የማረሚያ ቤቱ የደህንነት አባላት ባሳዩት ከፍተኛ ሙያዊ ክህሎትና ንቁ ክትትል የተሸሸገውን ህገ-ወጥ ዕፅ በፍተሻ ወቅት ማጋለጥ ችለዋል። የሣውላ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ታረቀኝ አጥናፉ እንደገለጹት፤ የታራሚ ዘመድ ጠያቂዎች የህግ ታራሚዎችን በማነፅና በማረም ሂደት ውስጥ አጋዥ መሆን ሲገባቸው መሰል አነዋሪ ተግባራት ላይ መሰማራታቸው ተገቢ አይደለም።…
Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗