ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ

ADDIS_REPORTERneutral2026-08-18 09:32:36 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ አረቄ ተደፋ ​በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ የሆነና ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ህገ-ወጥ የሀበሻ አረቄ በቁጥጥር ስር ውሎ እንዲደፋ ተደረገ። ​የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ሳጅን ጌታሁን ክፍሌ እንደገለጹት፤ ህገ-ወጥ አረቄ ማዘጋጀትና ማሰራጨት ለጤና ጉዳትና ለወንጀል መበራከት መንስኤ በመሆኑ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት ከጸጥታ አካላት ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል። መረጃው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]