ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ህገ-ወጥ የአበሻ አረቄ ተወገደ
ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያለው ህገ-ወጥ የአበሻ አረቄ ተወገደ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ለወንጀል መንስኤ ነው ተብሎ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ህገ-ወጥ የአበሻ አረቄ እንዲወገድ ተደርጓል ። ህብረተሰቡን ለጤና ጉዳት እና አካባቢውን ለሰላምና ደህንነት ስጋት የሚዳርገውን ህገ-ወጥ የአረቄ ምርትና ዝውውርን ለመቆጣጠር በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻና ክትትል ነው ምርቱ በቁጥጥር ስር የዋለው። በህገ-ወጥ መንገድ ተዘጋጅቶ ለዝውውር የቀረበው አረቄ በገበያ ዋጋ ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። የተያዘው ህገ-ወጥ ምርትም የህግ አግባብንና ግልጽነትን በተከተለ ሂደት በፖሊስ መርማሪዎች፣ በወረዳው አቃቤ ህግ፣ በቀበሌ…
Read the full story at zena24now ↗