የአሜሪካ መከላከያ ቡድን በ ኢትዮጵያ በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል ሥልጠና መስጠት ጀመረ!
የአሜሪካ መከላከያ ቡድን በ ኢትዮጵያ በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል ሥልጠና መስጠት ጀመረ! ኢትዮጵያና አሜሪካ በወታደራዊ መስክ በትብብር ለመስራት ያደረጉትን ስምምነት መሠረት በማድረግ መነሻውን ከሮድ አይላድ ያደረገው የአሜሪካ መከላከያ ቡድን በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል ሥልጠና መስጠት መጀመሩ ተገለፀ። መከለያ ሠራዊት እንዳስታወቀው ስልጠናው ትላንት ነሐሴ 11 ቀኝ የተጀመረ ሲሆን፣ በወታደራዊ ተልዕኮዎች ወቅት በሰብዓዊ መብቶችና ዓለም አቀፍ ወታደራዊ ሕጎች አጠባበቅ ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው። ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሠላም እየተጫወተች ላለው ሚና በርካታ አገራት በመሰል የሥልጠና ዘርፍ በትብብር እየሠሩ ነው ያለው መከላከያ ሠራዊት፤ አሜሪካም ከኢትዮጵያ ጋር ባደረገችው ስምምነት መሠረት የተለያዩ ሥልጠናዎችን በሁለትዮሽ ትብብር ለጋራ ተጠቃሚነት እየሰጠች ትገኛለች ብሏል።…
Read the full story at addis_news ↗