በድጋሚ የድሮን ጥቃት‼️
በድጋሚ የድሮን ጥቃት‼️ ከትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና ከመቀሌ 12 ኪሎሜትር እርቀት በምትገኘው እንደርታ ወረዳ፣ ኩሃ ቀዳማይ ወያኔ አካባቢ ዳንዴራ በተባለች መንደር ዛሬ ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም በድጋሚ ከቀኑ 10:10 አካባቢ የድሮን ጥቃት ተፈፅሟል። በዚሁ ቦታ ጠዋት 3:30 አካባቢ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ፣ ሌላ አንድ ታጣቂ ላይ ደግሞ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ የዓይን እማኞችን እና የአካባቢውን አስተዳደር ጠቅሶ ዘግቧል። ህወሃት በበኩሉ የፌዴራል መንግስቱ የድሮን ጥቃት ፈፅሞብናል ሲል የክስ መግለጫ አውጥቷል። አዩዘሀበሻ ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗