የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር ገባ

ADDIS_REPORTERneutral2026-08-18 16:41:55 UTC
AdYour ad here[email protected]

የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር ገባ የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል። የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጅ ቁጥር 1388/2017 መሰረት የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ቤት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደውን አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት መመሪያ ተዘጋጅቶ ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት መሆን የሚያስችለው አሰራር ወደ ተግባር መግባቱ ነው የተገለጸው፡፡ በመመሪያው መሰረት አንድ የውጭ ዜጋ ቢያንስ 150 ሺህ ዶላር ካፒታል ሊኖረው እንደሚገባ ተመላክቷል። በተጨማሪም በመንግሥት ድጎማ የተገነቡ ቤቶችን መግዛት እንደማይችሉም ነው የተገለጸው። @Addis_Reporter @Addis_Reporter

Read the full story at addis_reporter ↗
AdYour ad here[email protected]