የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት‼
የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት‼ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ግንኙነት በባሕር በር ጥያቄ እና በቀጣናዊ የደኅንነት ጉዳዮች ምክንያት መጠናት ክፉኛ እየተሻከረ መጥቷል። 📌 ኢትዮጵያ የባሕር በር መዳረሻ ጥያቄን በግንባር ቀደምነት ስታነሳ፤ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በበኩሉ "ወደብ የንግድ መዳረሻ እንጂ ከሉዓላዊነት ጋር አይያያዝም፤ ሉዓላዊነታችንም ለድርድር አይቀርብም" ሲል አቋሙን አስታውቋል። 📌 በኤርትራ እና በህወሓት መካከል ተፈጠረ የተባለው ትብብር በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አተገባበር ላይ ትልቅ ሥጋት ደቅኗል። 📌የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እና የደኅንነት ተመራማሪዎች የውስጥ የፖለቲካ ልዩነቶች ለውጭ ተጽዕኖ በር እንዳይከፍቱ መንግሥት ለውስጥ ሰላምና ለዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል።via DW #WasuMohammed video…
Read the full story at wasulife ↗