ትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ተነገረ
ትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ተነገረ በክልሉ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በ33 ሴቶች ላይ አሰቃቂ ግድያ መፈጸሙን የትግራይ ሴቶች ማህበር በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል። በክልሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየከፋ መምጣቱን የገለፁት የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ወ⁄ ሮ አበበ ሀይለስላሴ ለሁሉም የጥቃቱ ሰለባዎች ሚዛናዊ ፍትህ እንዲረጋገጥ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል። በክልሉ ፍትህን የሚጠብቁ በርካታ ተጎጂዎች እንዳሉ የጠቆሙት ስራ አስፈፃሚዋ፣ ህብረተሰቡ ለሁሉም የጥቃት ሰለባዎች እኩል ድምፅ በመሆን የፍትህ መዛባትን እንዲያወግዝ እና ወንጀልን የመከላከል ስራ ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ አሳስበዋል። ስራ አስፈጻሚዋ አክለውም ሃይማኖታዊ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን አጥብቀው…
Read the full story at zena24now ↗