በሀገራዊ ምክክሩ ለሠራተኞችና ለተማሪዎች ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ ሐሳቦች ቀርበዋል።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-19 14:38:47 UTC
AdYour ad here[email protected]

በሀገራዊ ምክክሩ ለሠራተኞችና ለተማሪዎች ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ ሐሳቦች ቀርበዋል። ከሐምሌ 8 ጀምሮ ሲመከርባቸው የነበሩ 96 ንዑስ አጀንዳዎች ዛሬ ለጉባኤተኞች ቀርበዋል! ከቀረቡት ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ፦ • ከደሞዝ ላይ የሚቀነሰው ግብር እንዲቀነስና ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እንዲወሰን ተጠይቋል። • ተማሪ ሴቶች በወር አበባ ምክንያት ከትምህርት እንዳይቀሩ የንጽሕና መጠበቂያ (Pad) በነጻ እንዲያገኙ የሚል ድንቅ ሐሳብ ቀርቧል። • መሬት የመንግሥት ብቻ መሆኑ ቀርቶ የግል፣ የወልና የመንግሥት እንዲሆንም ተመክሯል። እነዚህ ሐሳቦች ኑሮን ያቃልላሉ? ወይስ ወረቀት ላይ ብቻ ይቀራሉ? ሐሳባችሁን አጋሩኝ!"

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]