ናፖሊ ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ለማስፈረም ከስምምነት ለመድረስ መቃረቡ ተዘግቧል።
ናፖሊ ጋብሬል ጄሱስን ከአርሰናል ለማስፈረም ከስምምነት ለመድረስ መቃረቡ ተዘግቧል። የጣሊያኑ ክለብ ብራዚላዊዉን አጥቂ ማስፈረም ቢፈልግም ከጄሱስ ጋር ግን እስካሁን የደረሰበት ስምምነት የለም ተብሏል። ጄሱስ ለዝዉዉሩ ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል። አርሰናል ከተጨዋቹ 17 ሚሊዮን ፓዉንድ ይፈልጋል የተባለ ሲሆን ተጨዋቹ በአመት የሚከፈለዉ የ 5.2 ሚሊዮን ፓዉንድ ደሞዝ ግን ለናፖሊ ሊከብደዉ ይችላል ተብሏል። አርሰናል ተጨማሪ አጥቂ ለማስፈረም ከጋብሬል ጄሱስ በተጨማሪ ንዋኔሪ ፣ ፋቢዮ ቬራ እና ጋብሬል ማርቲኔሊን ለመሸጥ ያስባል። #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗