ዓለም አቀፍ የነዳጅ ሃያሏ ሩሲያ ከውጭ ነዳጅ ማስገባት ጀምራለች ተባለ!
ዓለም አቀፍ የነዳጅ ሃያሏ ሩሲያ ከውጭ ነዳጅ ማስገባት ጀምራለች ተባለ! የዓለም ግዙፏ የነዳጅ አምራች ሀገር ሩሲያ በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የተከሰተውን የነዳጅ እጥረትና የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሲባል ከውጭ ሀገራት ነዳጅ ማስገባት መጀመሯን የሀገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ መናገራቸውን የሀገሪቱ የዜና ወኪል ታስ (TASS) ዘግቧል። ሀገሪቱ ቀደም ሲል የሀገር ውስጥ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የነዳጅ ምርቶች ወደ ውጭ እንዳይወጡ እገዳ ጥላ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት ተጨማሪ ነዳጅ ከውጭ ለማስገባት ተገዳለች። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ አክለው እንዳመለከቱት፣ የመንግሥት አካላት በሀገር ውስጥ ያለውን የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ አስፈላጊውን ተጨማሪ እርምጃ ይወስዳሉ ነው የተባለው።…
Read the full story at addis_news ↗