የጋብቻ ጥያቄዬን አልተቀበለችም በማለት የጠለፋ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ9 ዓመት ጽኑ እስራትተቀጣ::
የጋብቻ ጥያቄዬን አልተቀበለችም በማለት የጠለፋ ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በ9 ዓመት ጽኑ እስራትተቀጣ:: በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ጎላ ቀበሌ ለጋብቻ ጥያቄው ፈቃደኛ ያልሆነችን ሴት በሃይል በመጥለፍ እና በመሰወር ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል። ተከሳሹ አቶ ገዛኸኝ ኃይለማርያም ነዋሪነቱ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጠንገጎ ቀበሌ ሲሆን የግል ተበዳይ የሆነችውን ሴት ለጋብቻ ይፈልጋት እንደነበር ተገልጿል። ግለሰቧ ግን ለጋብቻው ፍላጎት እንደሌላት በተደጋጋሚ ብትገልጽም ተከሳሹ ፈቃዷን ባለመቀበል ወንጀሉን ፈጽሟል። ሰኔ 30ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ ከምትኖርበት ከአሳግርት ወረዳ ጎላ ቀበሌ የጦ በተባለ አካባቢ፣ ተከሳሹ ከአምስት ያልተያዙ ግብረ አበሮቹ ጋር ሆኖ ከጠለፋት በኋላ ከሰዎች በመሰወር በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ይደብቋታል።…
Read the full story at zena24now ↗