በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የወርቅ ማዕድን ጉድጓድ ተደርምሶ የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ማለፉ ተገለጸ!
በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የወርቅ ማዕድን ጉድጓድ ተደርምሶ የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ማለፉ ተገለጸ! በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ምዕራባዊ ክፍል ከካሜሩን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው "ዛምቦዬ" በተባለ መንደር ባህላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ጉድጓድ ተደርምሶ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 ማለፉ ተገልጿል። በአደጋው ከተጎዱትና ህይወታቸውን ካጡት መካከል የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ዜጎች እና የጐረቤት ካሜሩን ዜጎች እንደሚገኙበት ተነግሯል። የአካባቢው ዓቃቤ ሕግ በአደጋው መንስኤ እና በማዕድን ማውጫው ሕጋዊነት ላይ ምርመራ መጀመሩን የገለጸ ሲሆን፣ በአካባቢው የነፍስ አድን እና የ አስከሬን የማውጣት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል። ቪዲዮ : ከማኅበራዊ ሚዲያ @tikvahethmagazine
Read the full story at tikvahethmagazine ↗