መኪናው ለተቃጠለበት አሽከስካሪ ከያንጎ መረቅ 300 ሺ ብር ድጋፍ ተደረገለት
መኪናው ለተቃጠለበት አሽከስካሪ ከያንጎ መረቅ 300 ሺ ብር ድጋፍ ተደረገለት በቅርቡ የመኪናው በወላፈን ሲቃጠል የሚያሳየው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭቶ የብዙዎችን ልብ መስበሩ ይታወቃል። ነገር ግን የዚህ አስከፊ አደጋ ሰለባ ለሆነው የያንጎ አሽከርካሪ አሁን ላይ ሁኔታዎች ተቀይረዋል። ያንጎ መረቅ (Yango By Mereq) አሽከርካሪውን በመፈለግ የ300,000 ብር የገንዘብ ስጦታ እንዲሁም አዲስ ዘመናዊ ስልክ አበርክቶለታል። ይህ አፋጣኝ ድጋፍ አሽከርካሪው ከገጠመው የሥራ መስተጓጎል በፍጥነት እንዲያገግም ትልቅ እፎይታ እንዲሆንለት በማሰብ የተበረከተ ነው። ይህ አጋጣሚ አስቸጋሪ ጊዜያትን ተጋግዞ ማለፍን የሚያሳይ ጭምር ነው። https://t.me/yango_by_mereq
Read the full story at tikvahethmagazine ↗