የህገ-ወጥ ጫኝና አወራጆች አሰራርን የሚገድብ ውሳኔ ተተላለፈ‼

WASULIFEneutral2026-08-21 08:36:51 UTC
AdYour ad here[email protected]

የህገ-ወጥ ጫኝና አወራጆች አሰራርን የሚገድብ ውሳኔ ተተላለፈ‼ ​በህገ-ወጥ ጫኝና አወራጆች የመማረር ቅሬታን ተከትሎ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በጥብቅ ውሳኔ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ ተገለፀ። ​በውሳኔው መሰረት ባለኑብረቱ ካልፈለገ በስተቀር በግዴታ ዕቃ የሚጭኑና የሚያወርዱ አካላት አገልግሎት መስጠት የማይችሉ ሲሆን፣ ፈቃድ ያላቸው ህጋዊ ጫኝና አወራጆችም አገልግሎት የሚሰጡት ከባለንብረቱ ጋር በሚደረግ ሙሉ ፈቃድና ስምምነት ብቻ እንደሆነ ተመልክቷል። ​ነዋሪዎች እቃቸውን በራሳቸው ማጓጓዝ ሲፈልጉ ያለአግባብ ገንዘብ እንዲከፍሉ መገደዳቸውና ለእንግልት መዳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ችግሩ በአዲስ አበባ፣ በአኦሮሚያና በሌሎችም ክልሎች የሚስተዋል በመሆኑ ተመሳሳይ ውሳኔ በመተግበር የዜጎች መብት እንዲከበር ጥሪ ቀርቧል።

Read the full story at wasulife ↗
AdYour ad here[email protected]