በናይጄሪያ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ADDIS_NEWSneutral2026-08-21 12:33:20 UTC
AdYour ad here[email protected]

በናይጄሪያ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ በናይጄሪያ ሰሜን-ምዕራብ ሶኮቶ ግዛት ከ70 በላይ ሰዎችን ይዛ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 48 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ፡፡ አደጋው የደረሰው ትናንት ጠዋት እንደሆነ የዘገበው ቢቢሲ፣ ተጎጂዎቹ በወንዙ ዳርቻ ወደሚገኙ የሩዝ እርሻዎቻቸው ለመሄድ በጀልባዋ ላይ እየተጓዙ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውታል፡፡ በአደጋው ከ70 በላይ ሰዎች በጀልባዋ ላይ እንደነበሩ ሲገመት፣ እስካሁን ወደ 10 የሚጠጉ ሰዎች በሕይወት መትረፋቸው ተነግሯል። በአደጋው ከሞቱት መካከል በርካቶቹ ሕፃናት እንደሆኑም አካባቢውን የሚወክሉ የፓርላማ አባል መናገራቸውም በዘገባው ተመላክቷል። ጀልባዋ ከአቅም በላይ ጭና እንደነበርና በጀልባዋ ላይ በነበረው ቀዳዳ ስፍራ ውሃ ወደ ውስጥ በማስገባቱ አደጋው መከሰቱን የሀገሪተ ባለሥልጣናት…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]