ሰሜን ወሎ፤ መንገድ ላይ በተቀበረ የፀረ ተሽከርካሪ ምክንያት የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ!
ሰሜን ወሎ፤ መንገድ ላይ በተቀበረ የፀረ ተሽከርካሪ ምክንያት የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ! በሰሜን ወሎ ዞን አንጎት ወረዳ ከተረፌ ወደ አሁን ተገኝ ላይ ሰባት ሰዎችን ጭኖ በሚጓዝ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ ላይ የተቀበረ ፈንጂ ፈንድቶ የአራትት ሰዎች ሕይወት አለፈ፣ ሦስት ሰዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደረሰባቸዉ። ሰባት ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረዉ ባጃች የተቀበረዉ ፈንጂ የፈነዳበት አንጎት ወረዳ 010 ቀበሌ አኖሬ ሁዳድ ከሚባል ቦታ ላይ መሆኑን የአንጎት ወረዳ መንግስት ኮሚዮኒኬሽን ጵ/ ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉወርቅ ጫኔ ተናግረዋል። አደጋዉ የደረሰዉ ማክሰኞ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ መሆኑም ታዉቋል።አካባቢዉ የፀጥታ ችግር ያለበት መሆኑን ያነሱት ኃላፊዋ በፍንዳታዉ የሞቱት ሁሉም ንፁኃን መሆናቸዉን ተናግረዋል። Via DW @Addis_News…
Read the full story at addis_news ↗