ሶለል የራያ መድመቂያ፣ የማንነት ማሳያ
ሶለል የራያ መድመቂያ፣ የማንነት ማሳያ የሶለል በዓል በሰሜን ወሎ ዞን ራያ “ባሕል ድልድያችን፣ አንድነት መዳረሻችን” በሚል መሪ መልዕክት በድምቀት ተከብሯል። በዓሉ የራያ ሕዝብ ባሕላዊ እሴቶችን፣ ትውፊቶችን እና የአንድነት መንፈስን የሚያጠናከር ነው። የራያ ቆቦ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ መኮነን አጥናፉ በዓሉ የራያ ባሕላዊ ማንነትን ከማስተዋወቅ ባለፈ የማኅበራዊ አንድነትን፣ መተሳሰብን እና አብሮነትን የሚያጠናክር ጠንካራ ባሕላዊ እሴት መኾኑን ገልጸዋል። የባሕል ውርስን ለትውልድ በማስተላለፍ፣ የሕዝቦችን አንድነት እና አብሮነት ማጠናከር እንደሚገባ ተመላክቷል።
Read the full story at amharamassmedia ↗