የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት
የሀገራዊ ምክክር ጉባዔው የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት በ4 ሺህ ተመካካሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር እንዲሁም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ተገኝተዋል፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ እና የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ኮሚሽነሮችና የምክክር ጉባዔው ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ @Addis_News @Addis_News
Read the full story at addis_news ↗