የምክክር ኮሚሽኑ ከወር በላይ የቆየው የምክክር ጉባዔ ዛሬ መጠናቀቁን አስታወቀ።

TIKVAHETHIOPIAneutral2026-08-22 13:42:19 UTC
AdYour ad here[email protected]

የምክክር ኮሚሽኑ ከወር በላይ የቆየው የምክክር ጉባዔ ዛሬ መጠናቀቁን አስታወቀ። በኮንቬንሽን ማዕከል ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም በይፋ የተጀመው የምክክር ጉባዔ የምክክር ሂደት በዛሬው እለት በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ሀገራዋዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ሒሩት ገብረስላሴ በሰጡት መግለጫ፣ "በእነዚህ ቀናት 4 ሺሕ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ በመሰባሰብ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ስምንት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ሲመካከሩ ቆይተዋል" ብለዋል። "ተመካካሪዎቹ ለዘመናት ለቆዩ አለመግባባቶች መፍትሄ የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን አጠናክረው ለኮሚሽኑ አስረክበዋል" ብለዋል። "በሂደቱ ተመካካሪዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ በቀላሉ እየተግባቡ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ጊዜ ወስደው ጠንከር ያሉ ውይይቶችን እያደረጉ በመጨረሻ በአብዛኞቹ ጉዳዮች ላይ መግባባት ችለዋል" ነው ያሉት።…

Read the full story at tikvahethiopia ↗
AdYour ad here[email protected]