ጀኔራል ባጫ ደበሌ የአራት ዓመት የአምባሳደርነት ቆይታቸውን አጠናቀው በክብር ተሸኙ

NATNAELMEKONNEN21neutral2026-08-22 18:18:04 UTC
AdYour ad here[email protected]

ጀኔራል ባጫ ደበሌ የአራት ዓመት የአምባሳደርነት ቆይታቸውን አጠናቀው በክብር ተሸኙ በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት ሙሉ ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ የአራት ዓመት የሥራ ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው ዛሬ በክብር ተሸኝተዋል። ጀኔራል ባጫ በኬንያ በነበራቸው የዲፕሎማሲ ቆይታ የኢትዮጵያና የኬንያን የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ሲሰሩ ቆይተዋል። በቀጣይም መንግሥት ጀኔራል ባጫ ደበሌን በሌላ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ለመመደብ እንደሚፈልግ ምንጮች ገልጸዋል። ሆኖም ስለቀጣይ ሹመታቸው እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም። የአራት ኮከብ ማዕረግ ያላቸውና የጥቁር አንበሳ ሜዳይ ተሸላሚ የሆኑት ሙሉ ጀኔራል ባጫ ደበሌ፣ በቀጣይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ሊሰጣቸው እንደሚችል ከምንጮች የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

Read the full story at natnaelmekonnen21 ↗
AdYour ad here[email protected]