“አይፎን 15” ካልገዛችሁልኝ ያለው ወጣት ራሱን ጨምሮ የቤተሰቡን ነፍስ ቀጥፏል።
“አይፎን 15” ካልገዛችሁልኝ ያለው ወጣት ራሱን ጨምሮ የቤተሰቡን ነፍስ ቀጥፏል። በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ዕድሜው 18 ዓመት የሆነ ወጣት አዲስ “አይፎን 15” (iPhone 15) ስልክ እንዲገዛለት ያነሳው ጥያቄ ቤተሰቦቹ ባለመቀበላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በመውጣት እራሱን ከገደል አፋፍ ላይ አቁሞ ቆይቷል። ወላጆቹ ለሰዓታት ሲለምኑት እና ለማሳመን ሲሞክሩ ከቆዩ በኋላ አባቱ ሊያድኑት ወደ እሱ ሲጠጉ፣ ወጣቱ አባቱን ጨብጦ በመሳቡ ሁለቱም ከገደል ወድቀው ህይዎታቸው አልፏል። ልጇን እና ባለቤቷን በድንገት ያጣችው እናቷም በደረሰባት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤ ከተመሳሳይ የገደል አፋፍ ላይ እራሷን በመጣሏ የሷም ህይወት ማለፉ ተዘግቧል። ይህ አሳዛኝ ክስተት በዛሬው ዕለት በርካቶች ሲመለከቱት፥ በወጣቶች የአዕምሮ ጤና ዙሪያ ያለውን ስጋት አጉልቶ ያሳየ ስለመሆኑ ተነግሯል።…
Read the full story at ayuzehabeshanews ↗