#ምስሎቻችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የአካባቢው አመራሮች ከየመንገዱ ያፈኗቸውን በርካታ ህፃናትና ወጣቶች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰዳቸው ታውቋል።

MESERETMEDIAneutral2026-08-23 11:54:11 UTC
AdYour ad here[email protected]

#ምስሎቻችን በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ወረዳ የአካባቢው አመራሮች ከየመንገዱ ያፈኗቸውን በርካታ ህፃናትና ወጣቶች ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋማት ባለፉት ጥቂት ቀናት መውሰዳቸው ታውቋል። "እነዚህ በምስሎቹ ላይ የሚታዩት ወጣቶች የመማርና የተሻለ ህይወት የመምራት ተስፋቸው ተቀጥፎ ወደ ጦር ግንባር እየተወሰዱ ነው፣ ህዝብ ይወቀው" በማለት አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል። በሌላ በኩል የአካባቢው ባለስልጣናት የሚዘውሯቸው የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች "በምዕራብ ጎጃም ዞን የቋሪት ከተማ ወጣቶች እና ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ ያለችን አንድ እናት ሃገር ኢትዮጲያ ናት፣ እሷንም ለማገልገል ዝግጁ ነን በማለት የሃገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ወደ ማሰልጠኛ በህብረተሰቡና በወረዳው አመራር ሽኚት ተደርጎላቸዋል" በማለት መረጃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

Read the full story at meseretmedia ↗
AdYour ad here[email protected]