ከጆኒ ጁጁትሱ ጋር ያደርገዋል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትግል ውድድር ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት፣ ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል አርት «ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል» በሚል ምክንያት ከውድድሩ ማለፉን ባሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል።

ADDIS_NEWSneutral2026-08-23 19:24:50 UTC
AdYour ad here[email protected]

ከጆኒ ጁጁትሱ ጋር ያደርገዋል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትግል ውድድር ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት፣ ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል አርት «ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል» በሚል ምክንያት ከውድድሩ ማለፉን ባሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል። ሴዶ ባስተላለፈው መልእክት፣ በተቃዋሚው ወገን በእንቁላል አማካኝነት ድግምት እንደተደረገበትና ንቃተ ህሊናንም ያሸነፈው በዚሁ ሁኔታ መሆኑን ገልጾ፣ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቶ መወዳደር እንደማይፈልግ አስታውቋል። ውድድሩን ለሚከታተለው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለትኬት ገዢዎች እና ለስፖንሰሮች ይቅርታ የጠየቀው ሴዶ፣ አዘጋጆቹ ሌላ ተወዳዳሪ ካቀረቡለት ለመግጠም ዝግጁ መሆኑን ጠቁሞ፣ የውድድር አዘጋጁን ኢቲኤፍሲ (ETFC) ቲሸርት በካሜራ ፊት አውልቆ በመጣል ከውድድሩ መውጣቱን አረጋግጧል። ሴዶ ይህንን መልዕክት ያስተላለፈው፤…

Read the full story at addis_news ↗
AdYour ad here[email protected]