የመንግስት ሆስፒታሎችን ከግል ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ማስተዳዳር ስለሚቻልበት መንገድ የሚመክር ውይይት ሊካሔድ እንደሆነ ተገለጸ
የመንግስት ሆስፒታሎችን ከግል ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር ማስተዳዳር ስለሚቻልበት መንገድ የሚመክር ውይይት ሊካሔድ እንደሆነ ተገለጸ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ ግዙፍ የመንግስት የህክምና ማዕከላትን የአገልግሎት ጥራት ለመጨመር ከ1 በላይ ዓለም አቀፍ የግል ኩባንያዎች ጋር በጥምረት ለማስተዳደር የሚያስችል ሰፊ ውይይት ሊካሄድ እንደሆነ ተገልጿል። የምስራቅ አፍሪካ ጤና ክብካቤ ፌደሬሽን እንዳስታወቀው፣ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 1 አህጉራዊ ጉባኤ ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ውይይት እና ስምምነት ይደረጋል። የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ዶክተር ማርቆስ ፈለቀ እንዳስታወቁት፣ መንግስት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ የገነባቸውን የህክምና ተቋማት በነባሩ አሰራር ብቻ መምራት ውጤታማ አያደርግም። በመሆኑም ተቋማቱ በቂ በጀት አግኝተው ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከግል ዘርፉ ጋር መስራት ወሳኝ አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል።…
Read the full story at addis_news ↗