በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እንደገለጸው፣ አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡ የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል የ5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡ ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡ #ዳጉ_ጆርናል
Read the full story at zena24now ↗