ተሽከርካሪን ሰሌዳ ነቅለው ህገወጥ ነዳጅ ሲያጓጉዙ የነበሩ 5 ግለሰቦች ተያዙ
ተሽከርካሪን ሰሌዳ ነቅለው ህገወጥ ነዳጅ ሲያጓጉዙ የነበሩ 5 ግለሰቦች ተያዙ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን ሀደሮ ጡንጦ ወረዳ በህገወጥ መንገድ ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የወረዳዉ ፖሊስ አስታውቋል። የክልሉ ፖሊስ የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ህገወጥ ነዳጁ በ18 ትላልቅና መካከለኛ ሮቶዎች እንዲሁም በ40 ፣በ25 እና በ20 ሊትር ጀሪካኖች የተጫነ ነው። የፊትና የኋላ ሰሌዳዎቹን ነቅሎ ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ነሀሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሌሊቱ 11፡30 አካባቢ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል። ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም የተሽከርካሪውን አሽከርካሪ ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቋል። የሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ነዳጁ ከየት እንደተጫነና ወዴት…
Read the full story at addis_news ↗