የትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ራሳቸውን ወደ ማስተዳደር ለመሸጋገር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሃብት ዕገዳ ጣለ
የትምህርት ሚኒስቴር ሙሉ ራሳቸውን ወደ ማስተዳደር ለመሸጋገር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ በሚገኙ ዘጠኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሃብት ዕገዳ ጣለ በሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ የተፈረመው ውሳኔ ዩኒቨርሲቲዎቹ ንብረት እንዳይሸጡ፣ በሃብታቸው እንዳይበደሩ እና ትልልቅ የኮንስትራክሽንና የግዥ ውሎችን እንዳይፈፅሙ ያግዳል። አሰራሩ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅና የአዲሶቹ አመራሮች ስልጣን እስኪረጋገጥ ጥንቃቄ ለማድረግ የተወሰደ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል። ዕገዳው የተጣለባቸው ዩኒቨርሲቲዎች፡ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ መቐለ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ፣ ሀረማያ፣ አርባ ምንጭ፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ASTU) እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (AASTU) ናቸው። ሚኒስቴሩ በጅማ፣ ጎንደርና AASTU የነበሩ አመራሮችን በማዛወር ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቶችን የሾመ ሲሆን፣ በቀጣይ በውድድር ለመመደብ አቅዷል።…
Read the full story at addis_reporter ↗