ጷጉሜን ከስራ እረፍት በማድረግ የፌስቲቫል ወር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተነገረ

ZENA24NOWneutral2026-08-24 15:34:51 UTC
AdYour ad here[email protected]

ጷጉሜን ከስራ እረፍት በማድረግ የፌስቲቫል ወር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተነገረ በጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ማህበር አማካኝነት ላለፉት 8 ዓመታት በደማቅ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየዉ የጷጉሜ ፌስቲቫል ዘንድሮም ለየት ባለ ሁኔታ ለ9ኛ ጊዜ ጷጉሜ የአፍሪካ ወርቃማ ወር በሚል መሪ ቃል በአፍሪካ ህብረት ግቢ ዉስጥ ከጷጉሜ 2 እስከ 5 እንደሚካሄድ ተገልጿል ። የኢትዮጵያዉያን ብቻ በሆነዉ ጷጉሜ ወር የሚካሄደዉ ይህ ፌስቲቫል ሀገራችንን የቱሪስት መዳረሻ በማድረግ የእርስ በርስ ትስስር ማጠናከር እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ዋናዉ ዓላማ መሆኑን የጳጉሜ አብ ፌስቲቫል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ሃይለአብ መረሳ መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ። የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችን የሚወክሉ አመጋገብ ፣ጭፈራ እንዲሁም እንደ ደራሮ ፣እሬቻ እና ሬራና የመሳሰሉ የአዲስ ዓመት አከባበር ስነ ስርዓቶችን…

Read the full story at zena24now ↗
AdYour ad here[email protected]