መውሊድ‼
መውሊድ‼ ነገ ማክሰኞ 1,501ኛው የነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሀገራችን በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል። 📌 የዘንድሮው መሪ ቃል፦ "የፍትሃዊው ነብይ" በዓሉ የነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮ መሠረት በማድረግ በተለያዩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ መርሐ-ግብሮች ይከበራል። መውሊድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ ሆነው ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ በዓላት አንዱ ነው። ፡፡ ነገ የሚከበረውን የመውሊድ በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ መልካም የመውሊድ በዓል!
Read the full story at addis_reporter ↗